The following text field will produce suggestions that follow it as you type.

God is my Shepherd
God is my Shepherd

God is my Shepherd

Current price: $5.99
Loading Inventory...
Get it at Barnes and Noble

Size: OS

Get it at Barnes and Noble
የእግዚአብሔር ስም አስደናቂ ስም ነው። "ስምህ ይቀደስ የሚለው" ጸሎት አንዱ የጸሎት ትርጉም ስሙን ከማስተዋል እንደሚመነጭ የሚነግረን ነው። እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠራባቸው ስሞች አሉ። እነዚህ ስሞች የራሳቸው ትርጉም ያላቸውና እግዚአብሔርን በመረዳት በኩል የሚሰጡን ልዩ ትርጉም አለ። ስሙን ማስተዋላችን ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት የተሳመጠ (intimate) ያደርገዋል። በዚህ መሳመጥ ውስጥ እግዚአብሔርን መለማመድ አለ። በኒውማ ጽሑፍ የእግዚአብሔርን ስሞች በተመለከተ የቀረቡ ተከታታይ ጽሑፎች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ያህዌ ይርኤ፣ ያህዌ ሻሎም፣ ያህዌ ንሲ የሚሉት ይገኙበታል። እነዚህ ሦስት የስሙ ትርጉሞችና ልምምዶች ከዚህ በፊት በወጣው "ያህዌ ንሲ- በዓላማ መኖር" በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ታትመው ለአንባቢ ቀርበዋል። አሁን ደግሞ "ያህዌ ሮኢ - እግዚአብሔር እረኛዬ" በሚለው በዚህ መጽሐፍ የእግዚአብሔርን እረኝነት በተመለከተ የጋራና የግል ልምምዶቻችንን የሚያጎለብቱ ጽሑፎች ቀርበዋል። እግዚአብሔር "እኔ . . . ነኝ" መሆኑን በኢየሱስ ነው ያሳየው። እርሱ በኢየሱስ ሰው የሚያስፈልገውን ሁሉ ሆኖ መጣ። አሁን ትኩረታችንን የሚስበውና በመተንተን የምንመለከተው "መልካም እረኛ እኔ ነኝ" የሚለውን ይሆናል። "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው" የሚለው በዕብራይስጥ "ያህዌ ሮኢ" ይባላል። የእግዚአብሔር እረኝነት የተገለጠው በጌታ ኢየሱስ ነው። እኛ እንደ በጎች እርሱ ደግሞ እንደ መልካም እረኛ ነው። የእርሱን እረኝነት በኑሮአችን ልንለማመደው ይገባል።
Powered by Adeptmind