The following text field will produce suggestions that follow it as you type.

?????? ?????
?????? ?????

?????? ?????

Current price: $53.00
Loading Inventory...
Get it at Barnes and Noble

Size: OS

Get it at Barnes and Noble
በዚህ "የኢትዮጵያ ፈተናዎች" የሚል ስያሜ በተሰጠው መድብል ውስጥ የተካተቱ ጽሁፎች ጉልህ የሆኑ ሃገራዊ ፈተናዎቻችንን ይዳስሳሉ። ጽሁፎቹ ባለፉት ፪ አመታት ውስጥ የተከተቡ ናቸው። በአመዛኙ ያልሰነበቱ ሃገራዊ ችግሮቻችን ላይ ያተኩራሉ። ቸል የማይባሉ እድሜ ጠገብ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ውጣ ውረዶቻችንንም በወጉ ይቃኛሉ። የጽሁፎቹ አንኳር አላማ ለችግሮቻችን ሁሉ ተጠያቂ አካል ማፈላለግ አሊያም ለገጠሙን ውስብስብ ሃገራዊ ፈተናዎች መንስኤ እንደሆኑ የሚታመኑ ወገኖች ላይ ጣት መቀሰር አይደለም። ይልቁንም ከትላንት ግድፈቶቻችን ተምረን ነጋችንን ብሩህ ማድረግ የሚያስችሉ የመፍትሄ ምክረ ሃሳቦችን ማመላከት ነው። የምክረ ሃሳቦቹም ጭብጥ ኢትዮጵያ ጸጋ አልቦ ሃገር አለመሆኗን ከመረዳት ይመነጫል። ጽሁፎቹ እውቀትን፣ ማስረጃን፣ ጠንካራ አመክንዮን፣ እና ምሁራዊ ተአማኒነትን መሰረት ያደረጉ ናቸው። የጽሁፎቹ ሙግትም ከሃገረ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ወገንተኝነት ይቀዳል። በጥቅሉ ጽሁፎቹ የጸሃፊውን ጠንካራ ሃገር የማየት ህልም ለማንጸባረቅ ብርቱ ሙከራ አድርገዋል።
Powered by Adeptmind